This page contains information about the Office of Contracting and Procurement for Amharic speakers.
የተልዕኮ መግለጫ፡-
የውልና ግዥ ጽሕፈት ቤት (OCP) ተልዕኮ ሁሉም የግዥ እንቅስቃሴዎች ፍትሐዊና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መከናወናቸውን በማረጋገጥ ጥራት ያላቸው እቃዎችንና አገልግሎቶችን በፍጥነትና በሚዛናዊ ዋጋ በመግዛት ረገድ ከአገልግሎትና ሸቀጥ አቅራቢዎች እና ከዲስትሪክት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር በአጋርነት መስራት ነው።
የስራ ክፍል ዋነኛ ፕሮግራሞች/መግለጫ፡-
የውልና ግዥ ጽሕፈት ቤት (OCP) የደንበኞች መስተንግዶ ማእከል የተቋቋመበት ዓላማ በአንድ ግዜ ግንኙነት ለጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ከአገልግሎትና ምርት አቅራቢዎችና ኤጅንሲዎች ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖር ጥረት እያደረገ አገልግሎት መስጠት ነው። አስተማማኝ ድጋፍ ለመፍጠርና ለሁሉም የስልክ ጥሪዎች፣ ኢሜይሎችና ደብዳቤዎች መልስ በመስጠት የመረጃ መስመር በመሆን የስራ አጋሮቻችን ከፕሮግራሙ የሚፈልጉትን ነገር ለመገንዘብ ሁሉንም ጥረት እናደርጋለን።
አገልግሎቶች፡-
የአገልግሎትና ምርት አቅራቢ ስልጠና/ትምህርት
መስጠት የግዥ ስራ የሚገኝበት ደረጃን መከታተል
የኢሶርሲንግ ቴክኒካዊ እርዳታ
መስጠት የአገልግሎትና ምርት አቅራቢ ግንኙነቶች
የዲስትሪክት ግዥን በተመለከተ አቤቱታዎችን ማቅረብ
የትርጉም አገልግሎቶች፡-
የውልና ግዥ ጽሕፈት ቤትን (OCP) በተመለከተ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት እባክዎን በስልክ ቁጥር (202) 727-0252 በመደወል ጽሕፈት ቤታችንን ያነጋግሩ። ወደ ጽሕፈት ቤታችን ሲደውሉ ወይም ሲመጡ እርስዎን መርዳት እንድንችል የመስሪያ ቤታችን ሰራተኛ የሆነ ሰው ከአስተርጓሚ ጋር እንደሚያገናኝዎት ልናረጋግጥልዎት እንወዳለን።
የአድራሻ መረጃዎች፡-
የውልና ግዥ ጽሕፈት ቤትን (OCP) Office of Contracting and Procurement
የደንበኞች መስተንግዶ ማእከል Customer Contact Center
441 4ኛ መንገድ፣ ሰም፣ ህንጻ 700 ደቡብ 441 4th Street, NW; Suite 700 South
ዋሽንግተን ዲሲ 20001 Washington, DC 20001
ስልክ ቁጥር (202) 724-4477 Ph. No. (202) 724-4477
WEB: www.ocp.dc.gov WEB: www.ocp.dc.gov